ውድ የአቦል ቲቪ ቤተሰቦች
ናፈቋችሁ? እኔ ናፍቃችሁኝ ነበር ግን አታስቡ ዛሬ የአሻራን አስገራሚ ታሪክ እንድንወያይበት ሁሉንም አንገብጋቢ እውነት ይዜ መጥቻለሁ። የእኔ ቤተሰብ ችግር አለው ብዬ ሳስብ የአላዛርን ታሪክ አስታውስ እና ለቤተሰቤ ተመስገን እላለሁ። እነ አላዛር ሰሞኑን በጣም በድራማ ተጠምደዋል።
አላዛር በመጨረሻ ስለመጀመሪያ ቤተሰቡ አውቋል ግን ይሄ የሁለተኛ ቤተሰቡን ህይወት አመሰቃቅሏል። የተደበቁት ምስጢሮች ቀስ በቀስ ተጋልጠዋል። ማን ነው ትክክል? ማን ነው ጥፋተኛ?
አላዛር መጀመሪያ ከጋሽ ናንጌ ቤተሰብ ጋር መኖር ሲጀምር፣ ጋሽ ናንጌ ከሰፈሩ ሰው ወሬ እና አላዛርን ከመበጥበጥ ለመከላከል ብለው የጓደኛዬ ልጅ ነህ አሉት። ይሄ በኋላ ላይ ችግር ይፈጥራል ብላቸሁ አስባችሁ ከነበረ እጃችሁን አውጡ! እሺ፣ ምንአልባት ጋሽ ናንጌ በዛ ሰአት ያለውን ችግር ለመፍታት ብቻ ነው ይሄን የተናገሩት ግን አንድ አመት አለፈ፣ ሁለት አመት አለፈ፣ ሶስት አመት አለፈ…አምስት አመት አለፈ፣ አላዛር ከምስር ጋር ልጅ ወለደ ግን እስካሁን እውነቱ አልተነገረውም።
አላዛር የጋሽ ናንጌ እና የሰፈሩን ሰው ህይወት አሻሽሏል ስለዚህ የድሮ ታሪኩ ቢረሳ ምንም ችግር የለውም አይደል? አይደለም! እንዴት ይሄ ይረሳል? አላዛርን ሲፈልገው ለኖረው ወንድሙ እና ካለአባት ላደገችው ልጁ ተገቢ አልነበረም። በአንድ በኩል ጋሽ ናንጌ እና ምስራቅ አላዛርን እየተከላከሉት መስሏቸው ነበር ግን ምስራቅ የአላዛርን ማንነት በድንገት ትደርስበታለች። ስለዚህ እውነቱን ትናገራለች ብለን እናስባለን አይደል? እሷ እንደዚህ አላሰበችም።
አላዛር ከእሷ ይነጠቃል የሚል ፍራቻ ገብቶባት ስለእሱ የሚያወራውን ጋዜጣ በጠቅላላ ትደብቃለች። በተጨማሪም ዜና ላይ ቀርቦ የግብርና ስራ የሚያቀል ስራውን እንዳያሳይ እና ቤተሰቡ ሊፈልገው እንዳይመጣ ልታስቆመው ትሞክራለች። ይህ ብቻ ሳይሆን ትልቁ ልጇ ጋዜጣውን አግኝቶ ሲጠይቃት ትዋሸዋልች። ነገር ግን ምስር ቤተሰቧ እንዳይበተን የምታደርገው ጥረት አልተሳካም እና ዮናስ አላዛርን ፍለጋ ደጃቸው ድረስ ይመጣል።
በቃ አሁን እውነቱን ትናገራለች ማለት ነው አይደል? አይደለም። ምስር ከመደንገጧ የተነሳ ዮናስን ለማስቆም ብትጥርም እውነቱ ይጋለጣል። እሁን አላዛር በሁለት ቤተሰቡ መሃል ተይዟል፣ እንዱ ቤተሰብ ስለማያውቀው ህይወት ይነግረዋል፣ በሌላ በኩል የሚያምነው ቤተሰብ ሲዋሸው ኖሯል። ይቅር ማለት ካልቻለ እኔ እረዳዋለው ግን አላዛር የመጀመሪያ ቤተሰቡን ለመተዋወቅ ወስኗል። ይህ ሁላችንንም አስገርሞናል ግን ከዚህ በኋላ የሚመጣው ይበልጥ አስገራሚ ነው ብዬ አምናልሁ። አላዛርን ገድለናል ብለው የሚያስቡት ሚስቱ ትዝታ እና ፍቅረኛዋ ማርቆስ አላዛርን ሊያገኙት ነው። አባቷን ለብዙ አመታት ያጣችው ልጁ ቤርሳቤህ ልታገኘው ነው።
ስለእናንተ አላውቅም ግን እኔ ፍንዲኛዬን አዘጋጅቼ የሚቀጥለውን ክፍል በጉጉት እየተጠባበቁ ነው።
አሻራ ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed