ሱራፌል የአባቱን ማንነት አውቋል። ሱራፌል ህይወቱን ሙሉ በውሸት የተመሰረተ ቅዠት ውስጥ ነበር የኖረው። ስለእናቱ ሞት እና አባቱ ማንነት ተዋሽቷል በተጨማሪም አሳዳጊው መስሎ የቀረበው አባቱ፣ በበቀል እና ክፋት የተሞላ ይህወት እንዲኖር አስገድዶታል። ሲያቅድ የኖረውን ነገር ሊያሳካ በደረሰበት ጊዜ ይህ ሁሉን እውነት ምዕራፍ በማጋለጧ ህይወቱ አደበላልቆታል። ስለዚህም ሱራፌል ተስፋ ቆርጦ ሞትን መምረጡ አስገራሚ አይደለም ግን ምዕራፍ እሱ እንደሚፈልገው ህይወቱን ማጥፈት የምትችል ይመስለዎታል?
ምዕራፍ የኪዳንን ነፃ ለማውጣት ምንም ነገር ከማድረግ ወድኋላ አትልም። ምዕራፍ የኪዳንን ማንነት አውቃ የረሳችውን የልጅነት ፍቅር ማስታወስ ከጀመረች በኋላ ህይወቷ ተመሰቃቅሏል። በዚህ ምክንያት የሱራፌልን ማንነት ደርሳበት ከሱ ጋር ያለመችው በፍቅር የተሞላ ህይወት ፈርሷል። ከዚህ ሁሉ በኋላ ከኪዳን ጋር ያላትን የፍቅር ግንኙነት ለመቀጠል ስትሞክር ሱራፌል ኪዳንን አታሎ በወንጀል እጁ እንዲጨማለቅ አድርጎታል። ኪዳንም በመኪና አደጋ ምክንያት ሆስፒታል ተኝቷል።
ምዕራፍ ለኪዳን ብላ ከታሪክ እና ህሊና ጋር ሱራፌልን ስታፈላልገው ቆይታለች። ከብዙ ጥረት በኋላ ህይወቷን ያበላሸው ሰው ህይወት በእጇ ወድቋል፣ ለበቀል ብላ ህይወቱን እሱ እንደፈለገው ታጠፋዋለች ወይስ የደህንነት መስራቤት ሰራተኞቹ በቁጥጥር ስር እንዲያውሉት ትረዳቸዋለች?
እርሶ በምዕራፍ ቦታ ቢሆኑ ምን ይመርጣሉ? በሱራፌል ቦታ ቢሆኑስ ስለአባቱ ውሸት እና የኖረው ህይወት ምን ይሰማዎታል? ቅጣቱ የሚገባ ነው ብለው ያስባሉ?
ተስፋ ስለቆረጠ ለመሞት ከሚፈልግ ሱራፊል እና በተደጋጋሚ ብትበደልም ተስፋ ላለመቁረጥ እየጣረች ካለችው ምዕራፍ መሀል ማን ያሸንፋል?
አስተያየቶን ኮመንት በማድረግ ያሳውቁን!
የዙረት ድራማ የመጨረሻ ክፍል ሰኞ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ ይተላለፋል!