channel logo
Yewha shita S1
channel logo

Yewhashita

465DramaPG13

አዲሱን የአቦል ቲቪ ድራማ የውሃ ሽታ ለመመልከት 5 ምክንያቶች

ዜና
29 ጃንዩወሪ 2024
የአቦል ቲቪ አዲሱ ልብ እንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ ጀምሯል።
yewha shita 5 reasons to watch article

የሞቷ ምክንያት በግልፅ የማይታወቀውን የፀሎትን ማስታወሻ ሮቤል የተባለ የሁለተኛ ዓመት የኮምፒዩተር ሳይንስ ተማሪ ያገኛል። ማስታወሻውን ተመርኩዞ የሞቷን ምክንያት ለማጣራት በሚያደርገው ጥረት የብዙ ተማሪዎችን ድብቅ ታሪክ በመገንዘብ በአካል ሊያገኛት ከማይችል ሟች ጋር በፍቅር ይወድቃል። ይሄን ምርጥ ታሪክ ለመመልከት እነዚህን ምክንያቶች እናቀርባለን፡

  1. ምርጥ ኮከቦቹ

የውሃ ሽታ ተወዳጅ እና ምርጥ ተወናዮችን ይዞ ይቀርባል። ሜላት ቴዎድሮስ፣ ማተብ፣ ትምኒት ገ/ኪዳን እና ሌሎች አስደናቂ ተዋናዮች በአዲሱ አቦል ቲቪ ድራማ ይቀርባሉ።

  1. ታሪኩ ምስጢራዊነት

መጀመሪያው ክፍል እንዳየነው ከሆነ የፀሎት ግደያ አልታወቀም ነገር ግን ጓደኛዋ ሜሮን በግድያው ጊዜ በቦታው ተገኝታ ነበር። የፀሎት ገዳይ ሜሮን ልትሆን ትችላለች ብለን ተጠራጥረናል ነገር ግን ሮቤል ያገኘው የፀሎት ማስታወሻ የተለየ ምስጢር ይዞ ሊቀርብ ይችላል። ይሄን ምስጢር ለመፍታት ማየት መቀጠል አለብን!

  1. ሚቀርብበት ሰዓት

ውሃ ሽታ ተከታታይ ድራማ የሚቀርበው ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 3፡00 ነው። የሳምንቱ አሪፍ መዝናኛ ሰዓት እና ቀን ላይ የሚቀርበው አስደናቂ ድራማ እንዳያመልጥዎ

  1. ገጸ ባህሪዎያቱ ልዩ ታሪኮች

መጀመሪያው ክፍል ልዩ ልዩ ገጸ ባህሪያትን ተዋውቀናል እነዚህ ገጸ ባህሪያት ግልጽ ያልሆነ ምስጢራዊ ህይወት እና መነሻ እንዳላቸው ተረድተናል። ለምሳሌ ሮቤል የፀሎት ገዳይ አለመያዙን ሲሰማ የገዳዩ መያዝ ቅድምያ መሰጠት እንዳለበት ነው የሚያምነው ይሄን ብሎ የሚያምነውም ይሄን ወንጀል በልጅነት ዕድሜው እናቱ ላይ ከደረሰው ጥቃት ጋር በማመሳሰሉ ነው። ስለ ሮቤል እናት ከፀሎት ግድያ ጋር የሚያገኘውን ምክንያት ለማወቅ በጉጉት እየተጠባበቅን ነው።

  1. ታሪኩ አቀራረብ

ሪኩ የሚቀርበው በሁለት አይነት ጊዜ ላይ ነው። የመጀመሪያው ጊዜ ፀሎት ከመሞቷ በፊት ሲሆን ሌላኛው ታሪክ ደግሞ ከሞተች በኋላ ነው። እነዚህን ሁለት ታሪኮች በማገጣጠም የፀሎትን ገዳይ ማወቅ እንችላለን።

እነዚህ ምክንያቶች የውሃ ሽታን እንዲመለከቱ እንዳሳመኗችሁ ተስፋ እናደርጋለን የውሃ ሽታ ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 3፡00 በ #አቦልቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት! #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed