ውድ ተመልካቾች
የበዓል - ለዛውም የአዲስ አመት በዓል - ጊዜ በጣም አጣዳፊ እና ወከባ የበዛበት ጊዜ እንደሆነ አውቃለሁ። ለቤተሰብ ምግብ ማዘጋጀት፣ ቤት ማስተካከል እና የመሳሰሉትን ስራዎች በምትሰሩበት ጊዜ፣ የትኛውን የአዲስ አመት መዝናኛ እንደምትመርጡ ለማሰብ ጊዜው እንደማይኖራችሁ እረዳለሁ። ግን ምንም ሀሳብ አይግባችሁ፣ እኔ ሲኒ፣ ለመላ ቤተሰባችሁ የሚመጥን መዝናኛዎችን መርጬ አቅርቤላችኋለሁ!
አዲሱ አመት በአዳዲስ መዝናኛዎች የተሞላ ነው።
አቦል ቲቪ አሁንም ጥራቱን የጠበቀ ሀገረኛ መዝናኛ ይዞልን መጥቷል! “የእሳት ዕራት” አዲሱ የቤተሰብ ድራማ ዒድና የተባለች የጠለፋ ሙከራ የተደረገባት ሴት ለ7 አመታት ከተሰወረች በኋላ ወደ ቤቷ ስትመለስ ያስቃኘናል። ሰለእናንተ አላውቅም ግን እኔ ስለ ዒድና ታሪክ ብዙ ጥያቄ አለኝ። መልሶቹን ድራማው መስከረም 20 ከምሽቱ 2:30 ሲጀምር እስከማውቅ በጉጉት እጠብቃለው።
አቦል ቲቪ ይሄን ብቻ አይደለም “የልቤ” የተባለ የፍቅር ታሪክም ያቀርብልናል። ስለእኔ አንድ ማወቅ ያለባችሁ ነገር ቢኖር የፍቅር ታሪኮችን በጣም ነው የምወደው! ይህ የፍቅር ታሪክ ደግሞ ለየት ባለ ቦታ ነው የሚተረከው፣ በጤና ሳይንስ የተመረቁት ጥንዶች ማርኮን እና ማህሌት በአምሮ ጤና ሆስፒታል ኢንተርን ሆነው መስራት ይጀምራሉ። ነገር ግን ጥንዶቻችን በፍቅራቸው ላይ ወድያው ፈተና ይደርስባቸዋል፣ ማህሌት ከሱፕርቫይዘሯ መቀራረብ ስትጀምር ማርኮን ደግሞ ከድሮ ጓደኛው እህት ጋር መቀራረብ ይጀምራል። ዋው! ይሄኛው ደግሞ ድራማው ብዙ እንደሆነ ያስታውቃል - መስከረም 17 ከምሽቱ 2፡00 እስከሚጀምር በጉጉት እጠብቃለሁ!
“ኮሜዲስ የታለ?” ብላችሁ ከጠየቃችሁ እንዳታስቡ ልላችሁ እፈልጋለው! አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት ኮሜዲ ድራማዎች መስከረም ላይ ይቀርባሉ። የመጀመሪያው የምናውቀው እና የምንወደው “እሽሩሩ” ድራማ በ 2ኛ ምዕራፍ ወደ አቦል ተመልሶ ይመጣል። ማን ይበልጥ እንደናፈቀኝ አላውቅም፣ አኩዬ፣ መላኩ፣ ዝናቤ ወይስ ይርገዱላሽ? እርስዎ ማንን በጉጉት ይጠብቃሉ? እሹሩሩ መስከረም 16 ከምሽቱ 3፡00 ይጀምራል!
ሁለተኛው ድራማ ደግሞ ታይቶ የማይታወቅ “አላውቅም አናውቅም” የተሰኘው ድራማ በሳታየር መልክ “ጭንቅ አዋላጅ” የሆኑት ሮዳ፣ ልያት እና አመቴን ልዩ ቀናት ያቀርባል። ከአቦል ቲቪ እንደሰማሁት ከሆነ አጋፋሪን የናፈቁት ተመልካቾች ይሄን ድራማ እጅግ በጣም ይወዱታል። እኔ ይሄን ብቻ ነው ማወቅ የሚያስፈልገኝ፣ አጋፋሪን የሚመስል ድራማ ለማየት ሁሌም ዝግጁ ነኝ! አላውቅም አናውቅም መስከረም 16 ከምሽቱ 2፡00 ይጀምራል!
የምንጠብቃቸው ብዙ ድራማዎች አሉ! በእነዚህ ድራማዎች እየተዝናናን መጠበቅ እንችላለን፡
በቅርብ ቀን የጀመረው ቴሌኖቬላ አሻራ ከቀን እስከ ቀን አዲሱን ክፍል ስጠብቅ በጉጉት ይናፍቀኛል! አስቡት በአንድ ጊዜ ሚስትን፣ ልጅን እና ስራን ማጣት ብቻ ሳይሆን የእራስን ማንነት ማስታወስ አለመቻል ምን ያህል ከባድ ነው? ዋናው ገጸ ባህሪያችን ይሄ ሁሉ በአንድ ቀን ደርሶበታል እናም ሚስቱ መዋሸቷን ቀጥላለች! በጣም የሚገርም ድራማ ነው እና አላዛር ማንነቱን ማስታወስ የሚችል ከሆነ ለማወቅ ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ እንከታተለው።
በ የረቂቅ መንገድ ረቂቅ እና አቶ ገዛህኝ የጂኤፍ ዋና ድርሻ ያዥ ለመሆን እየታገሉ ነው ነገር ግን ገዛህኝ ረቂቅ ልጁ መሆኗን አላወቀም። ረቂቅ ልጁ መሆኗን ቢደርስበት የሚቀበላት ይመስላችኋል? እኔ እርግጠኛ አደለሁም - በአንድ በኩል የረቂቅ እናት የገዛህኝ የመጀመሪያ ፍቅረኛው ስለሆነች እና ልጆቹን ስለሚወድ ሊቀበላት ይችላል ብዬ አስባለሁ። በሌላ በኩል ደግሞ የአቶ ገዛህኝን ጨቃኝነት እና ለሰው ህይወት ርህራሄ የሌለው እንደሆነ ሳስታውስ ጭራሽ ሊገላት ይችላል ብዬ አስባለሁ። የረቂቅን ታሪክ ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ ይከታተሉት!
ለኮሜዲ ጥማት ላላችሁ ደግሞ ምስኪኖቹ እና በምክንያት በየሳምንቱ ሀሙስ ከምሽቱ 2፡00 እና 2:30 እያዝናኑን ይገኛሉ! በተጨማሪም ልጆችን አልረሳናቸውም፣ አራቱ ጓደኞች እና ልደቴ የልጆች ፕሮግራም ቅዳሜ ጠዋት 4፡00 እና 4:30 ይቀርባሉ!
መልካም አዲስ አመት! - ሲኒ
አቦል ቲቪን በዲኤስቲቪ ፣ ቻናል 465 ያግኙት!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed