እስከዳር አፋፍን የእራሷ ለማድረግ ምንም ከማድረግ ወደ ኋላ የማትል ሴት ነበረች። ነገር ግን ለአፋፍ ካላት ምኞት በስተቀር ህይወቷ ፍጹም ነበረ፣ የሚወዳት ቤተሰብ እና ታላቅ መስራቤት ነበራት። የእስከዳር ህይወት መስመር የሳተው ለህልሟ ብላ በጭካኔ የጋሽ ዋሴን ህይወት ያጠፋች ቀን ነው።
ከዚያ ጊዜ በኋላ እራሷን ንጹ ማድረግ እና ፍትህ እንዲኖር ማድረግ የምትችልበት ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩ ግን እስከዳር በተደጋጋሚ የእራሷን ፍላጎት ከሁሉም ነገር በላይ አድርጋ መርጣለች። ለዚህ ሁሉ ስራዋ ምክንያት ያደረገችው በልጅነቷ ከአብዮት ጋር የወለደቻትን ልጇን አፋፍ ላይ ጥላ መሄድ ስለተገደደች ነው። ግን እስከዳር የዛን ጊዜ መከዳቷ ለዚህ ሁሉ ሰው ህይወት መበላሸት ምክንያት ይሆናል?
የእስከዳር አኗኗር የሚያሳየው የእሷ ህይወት ስለተበላሸ ህልሟን ለማሳካት የሌሎችን ሰዎች ህይወት ብታበላሽ ምንም ችግር የለውም ብላ እንደምታምን ነው። እነዚህ ሰዎች የጎዷት ግለሰቦች ሳይሆኑ፣ በመንገዷ የነበሩ ምንም የማያውቁ ሰዎች ናቸው።
እስከዳር የምትፈልገውን አገኛለው ብላ የጀመረችው ጨዋታ ፈልቶ ገንፍሏል።
- ባሏን ገድላዋለች።
- ልጆቿ ይጠሏታል።
- መስርያቤቷ ኪሳራ ላይ ነው።
ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን እስከዳር በቀልን መተው ስላልቻለች እዚህ ቦታ ላይ ደርሳለች። እንቆጳ የጣለቻት ልጇ መሆኗን ሳታውቅ ልትገላት ትሞክራለች ግን በዚህ ማሃል የምትጎዳው አጠገቧ የቆመው እንደ ልጇ ያሳደገችውን፣ ታምራትን ነው። ግን ይሄ አላስቆማትም ይሄንንም ጥፋት በእንቆጳ ላይ በማላከክ ልትገላት ውሀ ውስጥ ከታታለች። አብዮት እንቆጳን ለማዳን ሲል እንቆጳ ልጇ እንደሆነች ይነግራታል እናም ከውሀ ውስጥ አውጥታ ልታድናት ሞክራለች። ግን ይሄ ጊዜው ያለፈ ድርጊት ይመስላል፣ እንቆጳ ትተርፍ ይሆን?
እስከዳርስ፣ በግርግሩ ማሃል የት ጠፋች?
የእስከዳርን እና የአፋፍን ልብ እንጠልጣይ መጨረሻ ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!