channel logo
Yerekik menged S1

የረቂቅ ምርጫ ሁለት ነው፡ ነፍሰ ጡር ሴቷን መርዳት ወይም እራሷን ከአደጋ መከላከል

ዜና
03 ጁን 2024
ረቂቅ አስፈሪ ውጤት ሊያመጣ የሚችል ምርጫ ማድረግ አለባት፣ ምን ትመርጥ ይሆን?
yerekik menged article 2

ረቂቅ ተጽዕኖ ፈጣሪውን አቶ ገዛህኝን ለማጋለጥ አደገኛ ውሳኔ ወስናለች። ምንም እንኳን ይህን ለማድረግ ምክንያቷ ግልጽ ባይሆንም፣ አቶ ገዛህኝ ያለው ኃይል ሊኖረው የማይገባ አደገኛ ሰው መሆኑን ችላ ማለት አንችልም። አቶ ገዛህኝ በኩባንያው፣ በሥልጣኑ እና በቤተሰቡ ላይ ያተኮረ ነው፣ ከዚህ ውጪ የሆነ ነገር ሁሉ ለእሱ ስጋት ነው፣ ለዚህም ነው በዚያ መንገድ ላይ የሚገጥመውን ማንኛውንም ሰው ለማስወገድ ወደኋላ የማይለው።

ረቂቅ ወደ አቶ ዛህኝ ቤት ዘልቃ በመግባት ሹፌሩ በመሆን እጆቿን ታቆሽሻለች ነገር ግን ይህ ተሞክሮ ከጠበቀችው በላይ አስፈሪ ሆኗል አቶ ገዛህኝ የቀኝ እጁን ፊት ለፊቷ መግደል የወሰነው የተከዳ ስለመሰለው እና ረቂቅ ላይ የታማኝነት ፈተና ለመስጠት ነው። ረቂቅ ይህ ማስጠንቀቂያ እንደሆነ አውቃለች፣ ቀኝ እጁ በሆነው አበራ ላይ ይህን ማድረግ ከቻለ ቀጥሎ በእሷ እንዳይመጣ የሚያግደው ምንድን ነው?

ምንም እንኳን ይህ ቂቅን በውሳኔዋ እንድትደናቀፍ ቢያደርጋትም እሱን ለመሰለል ተልዕኮዋን አልተወችም ይህም ሣራን ያገኘችበት መንገድ ነው። ሣራ ከዓለም የተደበቀች የአቶ ገዛህኝ ነፍሰ ጡር ውሽማ ናት። ረቂቅ አቶ ገዛህኝን በፍቅር አለም ውስጥ ስታይ ሁሉም ደህና የሆነ ይመስላታል ነገር ግን ይህ ስሜት ከአቶ ገዛህኝ ሌላ የጭካኔ ባህሪ እስኪመጣ እንጂ ብዙም አይዘልቅም። አቶ ገዛህኝ የሣራ ልጅን የሚያዋልደው ዶክተር ሕፃኑ በሕይወት መትረፍ አለመቻሉን እንዲያረጋግጥ ሲያዝ ረቂቅ ትሰማለች።

በድጋሚ ረቂቅ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች እናም ምርጫ ማድረግ አለባት። ለአደጋ ተጋላጭ የሆነችውን ሣራን ከአደጋ ለማውጣት እና ልጇን ለማዳን ወይም እንደ አቶ ገዛህኝ ቀኝ እጅ አበራ ተመሳሳይ ዕጣ እንዳይደርስ እራሷን ለመጠበቅ?

Yerekik menged S1
yerekik menged poll 2

ረቂቅ ምን የምትመርጥ ይመስልዎታል?

ሳራን ትረዳታለች 100%
እራሷን ትጠብቃለች0%

#የረቂቅመንገድ ዛሬ ማታ 2:30 በ #አቦልቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!