channel logo
Gizze S1

ጊዜ፡ የህይወት ፈተና ሲበዛ እንዴት ይቋቋሙታል? የጀምበሩ ታሪክ

ዜና
25 ኦገስት 2023
የጀምበሩ ህይወት ከሀያ አመት በፊት በክህደት ተበላሽቷል። እዚህ እንዴት እንደደረሰ እንመልከት።
gizze jemberu article

ጀምበሩ ሁሉን ቻይ፣ አስተዋይ እና ይቅር ባይ ልብ ያለው ሰው ነው። የጀምበሩ ህይወት ፍጹም እና ሰው የሚቀናበት ነበር። ነገር ግን በጸሀፊው ግድያ ተጠርጥሮ እስርቤት ሲገባ ህይወቱ ይመሰቃቀላል። ባልፈፀመው ወንጀል ምክንያት 20 ዓመት ፍርዱን ጨርሶ ከእስር ሲወጣ ትዳሩ ተበትኖ ሚስቱ የገዛ ጓደኛውን አግብታ ትጠብቀዋለች። ከዚህም በተጨማሪ ልጆቹ ልእልና እና ምዕራፍ ነፍሰ ገዳይ ነው ብለው በማመናቸው ሊያገኙትም ሊያናግሩትም አልፈለጉም።

የሚወዳቸው ሰዎች አግልለውት በሚሄዱበት እና የሚረዳው ሰው ባጣበት ጊዜ ህሊና የተባለች ጠበቃ ከአጠገቡ ትቆማለች። ህሊና ጀምበሩን ከ20 አመት በፊት መርዳት ባለመቻሏ ያላት ጸጸት እና ድብቅ ፍቅሯ ተነሳስታ ጀምበሩን ለመርዳት ትሞክራለች። በተጨማሪም ተሻገር የተባለ ጋዜጠኛ፣ ልጅ እያለ ጀምበሩ ያደረገለትን እርዳታ ሳይረሳ ጀምበሩን ለመርዳት ይሞክራል።

ጀምበሩን ለመርዳት የሚፈልጉ ሰዎች በአካባቢው ቢኖሩም ሊያጠቁት የሚፈልጉት ሰዎች ግን ይበዛሉ። የድሮ ቅርብ ጓደኛው ጌታቸው የጀምበሩን ሚስት ያገባው የጀምበሩ እስርቤት መግባት ተከትሎ ነው። ጀምበሩ እስርቤት ከወጣም በኋላ ህይወቱን ይበልጥ ለማክበድ እና አክሲዮን የተባለው ኩባንያውን በእጁ ለማስቀረት ጀምበሩን ለማስወገድ ይሞክራል። ከዚህም በተጨማሪ የሟች ወንድም ታሪኩ ጀምበሩን አጥፍቶ የህቱን ገዳይ ለመበቀል ይሞክራል።

ጀምበሩ በዚህ ሁሉ መሀል እራሱን ከሰው አግልሎ ከአንድ አቡሽ የተባለ ህጻን ጋር ጎዳና ላይ ይኖራል። እርስዎ ጀምበሩ ሊረዱት የሚፈልጉት ሰዎችን እርዳታ ሳይቀበል እራሱን እየጎዳ መኖር መምረጡን መረዳት ይችላሉ? በህወታችን ውስጥ ሁሉም ነገር ሲከፋ ከሰው ተነጥለን ብቻችንን የችግሩን መንስኤ ለማግኘት ጥረት ብናደርግ የመሳካት እድል አለው?

Gizze S1 poll
ምርጫዎን ያሳውቁን

እርስዎ በጀምበሩ ውሳኔ ይስማማሉ?

አዎ እስማማለሁ88%
አይ አልስማማም13%

የጀምበሩን መሳጭ ታሪክ ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!