የልቤ ሜዲካል ድራማ በሁለት ጥንዶች ህይወት እና ግንኙነት ላይ የሚያጠነጥን ነው። ጥንዶቹ ታሪካቸው በጣም ልዩ ቢሆንም፣ አንድ አንድ ባህሪ እና ድርጊቶች ያመሳስሏቸዋል። የማኪ እና ኤርሚያስ ትዳር ጥሩ መሰረት ነበረው፣ ነገር ግን የኤርሚያስ ቅናት የማኪን ህይወት አደጋ ውስጥ ከቷል። በሌላ በኩል ማህሌት የመጀመሪያ አመት ዩኒቨርሰቲ ተማሪ እያለች ብሩክ በግድ ፍቅረኛው እንድትሆን ሊያደርጋት ሲሞክር ማርኮን አድኗታል። በዚህም የተነሳ ማህሌት እና ማርኮን በፍቅር ወድቀው ግንኙነታቸውን ቀጥለዋል። ነገር ግን ብሩክ አሁን የማህሌት ሱፐርቫይዘር ሆኖ ወደ ህይወቷ ተመልሷል። በዚህ ምክንያት በግንኙነታቸው ብዙ ቀይ ካርድ የሚያሰጡ ነገሮች ነበሩ።
ማኪ እና ኤርሚያስ
- ማኪ ከሌላ ወንድ ጋር ለስራ ስለተነጋገረች ኤርሚያስ መቅናት ይጀምራል። ይሄ ቀይ ካርድ ያሰጣል ምክንያቱም ይህ ቅናት የመነጨው ማህሌት መቆጣጠር ከምትችለው ኣካል አይደለም።
- ማኪ ከጓደኞቿ ጋር ስትዝናና እና ወደ ሱቅ ስትሄድ ኤርሚያስ ታማኝነቷን ይጠራጠራል። ይህ ቀይ ካርድ ያሰጣል ምክንያቱም ባለትዳር መሆን ከሌላ ሰው ጋር ግንኙነት ማቆም አለብን ማለት አይደለም።
- ኤርሚያስ ምክንያት የሌላቸውን ጥርጣሬዎች ከማኪ ጋር ተነጋግሮ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ በንዴት ማኪን ይደበድባታል። ይህ ቀይ ካርድ ያሰጣል። ይህ ትዳር የሚያፈርስ ድርጊት ነው ምክንያቱም ትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮች በንግግር መፈታት እንጂ መደብደብ ትክክል አይደለም።
ማህሌት እና ማርኮን
- ማህሌት በስራ በኩል የምታገኘው አድቫዘርዋ ብሩክ እንደማትፈልገው እያወቀ ከስራ አልፎ ሌላ ግንኙነት ለመፍጠር ይሞክራል። ይህ ቀይ ካርድ ያሰጣል።
- ማህሌት ማርኮንን ለማስደሰት ብላ ብሩክ እያስጨነቃት እንደሆነ ትደብቀዋለች። ይህ ቀይ ካርድ የሚያሰጠው የማህሌትን ህይወት አደጋ ውስጥ ስለሚከት እና ችግሩን አብረው መፍታት ስላለባቸው ነው።
እነዚህ በፍቅር ግንኙነት ላይ ቀይ ካርድ የሚያሰጡ ነገሮች ናቸው። እናንተ በድራማው ያስተዋላችሁት ሌላ ቀይ ካርፍ የሚያሰጥ ድርጊት ነበር? በማህበራዊ ሚዲያ ኮሜንት በማድረግ ያሳውቁን!
የእነዚህን ሁለት ጥንዶች መጨረሻ በየልቤ ዘወትር አርብ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት።
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed