channel logo
Afaf S1

አፋፍ: አሁን ምን ላይ ደርሰዋል?

ዜና
27 ጁን 2024
አፋፍ ድራማ ከሰኞ ፣ ሰኔ 17 ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ በአቦል ቲቪ ይቀርባል።
afaf mon - wed article

የአፋፍ ድራማ ገጸ ባህሪያት በብዙ ውጣ ውረድ አልፈው ያልጠበቅነው ቦታ ደርሰዋል። የእስከዳር ቤተሰብ ተከፋፍሎ ድርጅቷ በኪሳራ ውስጥ ይገኛል። እስከዳር ከዚህ የሚያስጠላ መንፈስ ለማገገም እና በእርሷ ላይ በደል በፈጸሙ ሰዎች ላይ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ወሰነች። በተጨማሪም ከድብርት ጋር የሚታገለውን ታምራት ለመርዳት ትታገላለች፣ ይህ ትግል ከጭንቀቷ ለማገገም እና ወደ ቀድሞ ጥንካሬዋ ለመመለስ ይረዳት ይሆን?

እንቆጳ በሕግም ሆነ በሥነ ምግባር እስከዳርን ለመዋጋት መሞከሯ ዋጋ እንደሌለው በመገንዘቧ ተስፋ ቆርጣለች። ነገር ግን እንቆጳ ታምራትን ደጋፊዋ እንዲሆን የሚያስችላትን ሁሉ ለማድረግ ወሰናለች፣ ለዚህ ውሳኔ ዋና ምክንያቷ የተደበቁት ነገሮች ቁልፉ ላይ ለመድረስ እሱን የቀኝ እጅዋ ማድረግ ነው ብላ ታምናለች። ጥረቷ ይሳካ ይሆን?

በሌላ በኩል ደግሞ አብዮት የልጁን ዕጣ ፈንታ ለመረዳት ሲሞክር፣ ሽቱ እንቆጳ የአብዮት ልጅ መሆኗን ደብቃ ለመኖር እየታገለች ነው። ሽቱ ስለ እንቆጳ ወላጆች የምታውቀው እውነት የሁሉምን ገጻ ባህሪ ታሪክ የሚቀይር ነው። ስለዚህ ሽቱ እውነቱን መደበቋ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ? ሽቱ እንቀጳ እውነቱን ስታውቅ ትታት ትሄዳለች ብላ በማመኗ ነው መናገር ያልፈለገችው። ነገር ግን የብዙ ሰው ህይወትን የሚቀይር ምስጢር ሲሆን የደበቀችው፣ ስለዚህ ብቻ ማሰቧ ተገቢ ነው?

ይሄንን ትግል ማን ያሸንፍ ይሆን?

ያለፈውን ክፍል ይመልከቱ፡

አፋፍ ዘወትር ከሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት! በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed