አዲሱ የአቦል ቲቪ ድራማ አብሱማ በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ባህላዊ ልምዶች ላይ አዲስ እይታን ይዞ ይቀርባል። በመጀመሪያ፣ አብሱማ ምንድነው? አበሱማ በዋነኝነት በኢትዮጵያ አፋር ክልል ውስጥ የሚተገበር ባህላዊ ልምምድ ነው እና ስርአቱ የአጎት እና አክስት ልጆች እንዲጋቡ ይፈቅዳል። አሁን አብሱማ ምን እንደሆነ ካወቅን አዲሱን ትርኢት ምን አዲስ ነገር እንደሚያመጣ እንመልከት።
አብሱማ ፋጡማ “ፋፊ” የተባለች ወጣት የተማረች የአፋር ሴት የገጠር ህብረተሰቧን ሕይወት ለማሻሻ የምታደርገውን ጥረት ያሳያል። በዚህ ወቅት በአፋር ውስጥ በማህበረሰቡ ባህላዊ የጋብቻ ልምዶችን ለዲግሪው ምርምር እያደረገ ካለው ዘካርያስ ጋር ትገናኛለች። ዘካርያስ በፋፊ ተደንቆ ወዲያውኑ ከእሷ ፍቅር ይይዘዋል።
ነገር ግን ፋፊ በአፋር ወግ መሠረት ከአጎቷ ልጅ አብዶ ጋር ለመጋባት መታጨቷ ሁሉንም ነገር ያወሳስባል። አብዶ ፋፊን ማንም ከእሱ እንዲወስድበት አይፈቅድም ምክንያቱም እርሷ የእሱ ናት ብሎ ያምናል። ፋፊ ማህበረሰቡ ለራሳቸው የተሻለ ሕይወት እንዲኖሩ ለመርዳት የምታደርጋቸው ጥረቶች ሁለቱ ወንዶች ለእሷ ባላቸው ፍቅር ምክንያት የተወሳሰበ ይሆናል። ፋፊ ይህንን ተግዳሮት እንዴት ታሸንፋለች?
የአብሱማን የመጀመሪያ ክፍል ሰኞ መጋቢት 2 ከምሽቱ 3፡00 በ #አቦልቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ! በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed