የአሻራ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ከሰኞ - ረቡዕ በአቦል ቲቪ ይቀጥላል። በአላዛር መጥፋት ምክንያት በህይወቱ የነበሩት ሰዎች ተቀይረዋል። የእነዚህን ገጸ ባህሪዎች ባህሪ እንዳኝ፡
ትዝታ የአላዛርን አስክሬን ጫካ ከማርቆስ ጋር ከጣለችው በኋላ የተፈጠረውን እረስታ ህይወቷን ለመምራት ሞክራለች። ይሄን ለማድረግ የአላዛርን ትልቅ ፈጠራ ሸጣ በብሩ እንደፈለገች መኖር ጀምራለች።
ቤርሳቤህ ከአባቷ ሞት በኋላ ብቸኝነት ይሰማት ጀምሯል። እናቷ ትኩረት አትሰጣትም እና አጎቷ አልፎ አልፎ ብቻ ነው የሚያገኛት።
ዮናስ ከወንድሙ ሞት በኋላ ስለእራሱ ደንነት ማሰብ አቁሟል። በዚህ የተነሳ መጠጥ እና ሲጋራ ሱስ ሆኖበታል።
የእነዚህን ውስብስብ ገጸ ባህሪዎች ታሪክ በአሻራ ይከታተሉት። የአሻራ ልብ አንጠልጣይ ታሪክ ዘወትር ሰኞ - ረቡዕ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!