የረቂቅ እቅድ ቀላል ነበር። እናቷ እርጉዝ መሆኗን ሲያውቅ ከህይወቷ ያፈናቀላትን አባቷ አቶ ገዛህኝን መበቀል ትፈልግ ነበር። እናቷ ታማ ለሆስፒታል ክፍያ አጥታ መሞቷ ለዚህ በቀል ያነሳሳታል። አቶ ገዛህኝ የሶስት ልጆች አባት ነው እና የጂኤፍ ባለቤት ነው። እንደ መስራቤቱ የሚወደው ነገር የለም ስለዚህም ረቂቅ እሱን ለመጉዳት ብላ እራሷን ሹፌር አስመስላ መስራቤቱ ትቀጠራለች። ማሳካት የምትፈልገው ነገር አለ? አቶ ገዛህኝ የሚራራለትን ኩባንያ የእራሷ ማድረግ።
ምን አልባት እንዳሰበችው ቀላል እቅድ ላይሆን ይችላል ነገር ግን ሁሉም ነገር መስመሩን ይዞ እየሄደ ነበር። የረቂቅን ዕቅድ ከመስመር ያስወጧቸው ነገሮች እነዚህ ናቸው፦
- የአቶ ገዛህኝ ውሽማ። አቶ ገዛህኝ ነፍሰጡር ውሽማ ደብቆ ነበር። ነገር ግን እቅዷን የእሷን እናት ለመጉዳት እንደሞከረው የውሽማው ሳራን ልጅ ለመጉዳት ነበር። ስለዚህ ታሪክ እንዳይደገም ብላ ረቂቅ ሳራን እረድታታለች። ይህ ግን ከጎረቤቶቿ ጥያቄ እና ከአቶ ገዛህኝ ጥርጣሬ ነው ያመጣባት።
- በዚህ ምክንያት የተፈጠሩትን ጥያቄዎች ለመመለስ ስትሞክር የአቶ ገዛህኝ ሚስት ሳራን ማፈላለግ ትጀምራለች። አስቴር የእራሷን እቅድ ለማስፈጸም ስትጥር ስለ ሳራ ትሰማለች ግን ማንነቷን አታውቅም። ነገር ግን ጥርጣሬ ውስጥ ስለገባች ምርመራዋ ረቂቅ ጋር ይወስዳታል። ይህም ረቂቅ ልታሳርፋቸው የምትሞክራቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ይስባል።
- ለአቶ ገዛህኝ መስራት ያልጠበቀችው ግዴታዎችን ስለሚያካትቱ እቅዷን ለማሳካት አቶ ገዛህኝን ሊያታልሉ የተነሱ የስራ ባልደረባዎችን ማጋለጥ ይኖርባታል። ስራዋ ከአቶ ገዛህኝ ተቀባይነት ቢኖረውም የስራ ባልደረባዎቹ ደቦል እና መርከብ ቂም ይይዙባታል።
- ረቂቅ ይሄን ሁሉ ለማስተካከል እየሞከረች እያለች አቶ ገዛህኝ ከቤተሰቡ ጋር መኖር እንድትጀምር ያደርጋታል። በአንድ በኩል ይህ ከአቶ ገዛህኝ ስራ ጋር ያቀራርባታል ስለዚህ ጥሩ ነው ግን በሌላ በኩል ደግሞ በአባቷ በኩል ያላት ወንድሟ ዮናስ እንዲቀርባት እድል ይሰጠዋል። ዮናስ ረቂቅን መቅረቡ ችግር የሚሆነው እህቱ እንደሆነች ሳያውቅ የፍቅር ጥያቄውን እንድትቀበል ለማድረግ መነሳቱ ነው።
ረቂቅ በጥንቃቄ የገነባችው የውሸት ድር እንዳይፈርስባት ስትጥር ግን የሰው ነፍስ ለማጥፋት ተገዳ አታውቅም። ይህ ግን የኒና ምርቃት ቀን ይቀይራል። የፍቅር ጥያቄውን ባለመቀበሏ የተናደደው ዮሃንስ ከዝግጅቱ በኋላ አስገድዶ ሊደፍራት ሲል እራሷን ስትከላከል ነፍሱ በእጇ ይጠፋል። ከመደንገጧ የተነሳ ቤቱን ጥላ ስትጠፋ ተደብቀው ደካማ ጎኑን እስከሚያገኙ የሚጠብቁት ጠላቶቿ እርምጃ ይወስዳሉ። አሁን ረቂቅ በእጃቸው ገብታለች።
#የረቂቅመንገድ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30 በ #አቦልቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!