Logo
Serategna feligulin S1
channel logo

Serategna Feligulin

465ComedyPG13

በዚህ ዘመን ሰራተኛ ፍለጋ ይሄን ይመስላል - ሰራተኛ ፈልጉልን

ዜና
12 ጁላይ 2024
ሱዚ እና ዜና በየሳምንቱ ግራ የሚያጋባ ባህሪ ያላቸው ሰራተኞች ያጋጥሟቸዋል።
Serategna feligulin S1 article 1

ሰራተኛ ፈልጉልን አዲሱ የአቦል ቲቪ ኮሜዲ ድራማ ነው። ድራማው በባለትዳር ጥንዶች ጓዳ ውስጥ ያለውን አስቂኝ ጉድ ያቀርባል። ባል እና ሚስት ሱዚ እና ዜና የቤታቸውን ስራ እኩል መካፈል ባለመቻላቸው ሰራተኛ ለመቅጠር ይስማማሉ። ነገር ግን ጥሩ ሰራተኛ ማግኘት እና ማኖር ቀላል ነው ብለው በማሰባቸው ለሚገጥሟቸው ገጠመኞች አላዘጋጇቸውም። ሱዚ እና ዜና ቤት ከመጡት ሰራተኞች እኛ በእነዚህ ተዝናንተናል፦

1. እነዚህን ነገሮች ካላሟላችሁ መቅጠር አትችሉም!

1ኛ.  ደሞዝ ከጥቅማ ጥቅም ውጪ 10000 መጨመር።

2ኛ.  ፊትለፊቷ መቼም መጨቃጨቅ እንደማትችሉ መስማማት።

3ኛ.  አንድ ምግብ ለ15 ቀን መደገም እንደማይችል መስማማት።

ሱዚ እና ዜና እነዚህን ሶስት ነገሮች ካሟሉ እንዲቀጥሯት ይፈቀድላቸዋል። ነገር ግን ጥንዶቹ ምንም ከማለታቸው በፊት በስህተት እነሱ ቤት እንደተላከች ገብቷት ትሄዳለች።

Serategna feligulin S1
serategna feligulin S1 poll 2

እርስዎ ቢሆኑ እነዚህን ነገሮች ለሟማላት ይስማሙ ነበር?

መቼም አልስማማም71%
አዎ እስማማለሁ29%

2. የቤት አስቤዛችሁን ሳትቆልፉ ከቤት እንዳትወጡ!

ለሳምንት አስቤዛ ምን ያህል ብር ያወጣሉ? በአንድ ቀን አልቆ ቢያገኙት ምን ያደርጋሉ? ሱዚ ይህ ሲገጥማት እራሷን ለማመን አቅቷት ነበር። አይችሉሽም የተባለችው የቤት ሰራተኛ ወዲያው የጥንዶቹ ቤት እንደገባች ምግብ ብቻ መስራት ነው የያዘችው። በተጨማሪም ምግብ ካልቀመሰች የምትሞት ይመስላታል። ይህ ባህሪዋ በአንድ ቀን ውስጥ የቤቱን አስቤዛ እንድትጨርስ ያደርጋታል። ስለዚህም ጥንዶቹ የሚያስፈልጋትን ማሟላት ባለመቻላቸው ያሰናብቷታል።

3. ወንድ ሰራተኛም አለ!

ሱዚ ከባሏ ልጅ ለመውለድ የምታደርገው ጥረት ሊሳካላት አልቻለም እና ስለዚህ ከጓደኛዋ ጋር ሲወያዩ ዜናን በማስቀናት ልጅ ለመውለድ ፍቃደኛ ማስደረግ እንችላለን ብለው ያምናሉ። እናም ወንድ የቤት ሰራተኛ ሙሴ ቤታቸው እንዲቀጠር ያደርጋሉ። ልክ ሱዚ እንደጠበቀችው ዜና ቅናት ይሰማዋል፣ ከመቅናቱ የተነሳ ስለሱዚ እና ሙሴ ህልም ማየት ይጀምራል። ነገር ግን ሱዚ እንዳሰበችው የዜና ቅናት ልጅ እንዲፈልግ አላደረገውም። የሱዚ እቅድ ይከሽፋል ግን ባል እና ሚስት ይበልጥ ይቀራረባሉ።

Serategna feligulin S1
serategna feligulin S1 poll 3

እርስዎ እድሉ ቢገጥምዎ ወንድ የቤት ሰራተኛ ይቀጥራሉ?

አዎ ምን ችግር አለው50%
እኔ አይስማማኝም50%

ሱዚ እና ዜና የቤት ሰራተኛ ፍለጋቸውን ይቀጥላሉ። በሚቀጥለው ሳምንት ምን ይገጥማቸው ይሆን?

#ሰራተኛፈልጉልን ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይቀርባል!