channel logo
Hamza s1

ልጆቻችንን ለምን እናበላሻለን? የመኳንንት ታሪክ - ሀምዛ

ዜና
28 ጁን 2024
የአጥናፍ እና መኳንንት ስራ አካባቢያቸውን እንደዚህ ይረብሻል።
hamza mommy's boy article

በአንድ ገጠር ውስጥ የሚገኘው የጌቶች ቤት ውስጥ ያደገው መኳንንት በእናት እና አባቱ የሚመኘውን ሁሉ እንዲያገኝ ተደርጎ ያድጋል። አቻምየለው እና አጥናፍ መኳንንትን አንቀባረው ሲያሳድጉት የእርሱን እያንዳንዱን ፍላጐት ለማሟላት ያላቸውን ቁርጠኝነት ያልተጠበቁ መዘዞችን የሚያስከትል ጎዳና ላይ እንደሚመራቸው አያውቁም ነበር።

መኳንንት ስለራሱ ማራኪነት እና መብት ብቻ የሚያስብ ወጣት ነው። ስለዚህም በተለያዩ መንገዶች በአካባቢው ያሉትን ሰዎች ህይወት ሲያበላሽ ምንም ተጠያቂነት አይሰማውም። በአስተዳደጉ ምክንያት መኳንንት እስካሁን እንደዚህ አይነጥ ጥፋቶችን መስራት ችሏል፡

  1. የተጋነነ የመብት ስሜት በመጀመሪያ መኳንንት አለሜ የዳኜ እጮኛ ብትሆንም፣ እነሱን አለያይቶ አለሜ ሚስቱ ልትሆን ይገባል ብሎ ያምናል። ለዚህም እናቱን ጣልቃ በማስገባት የአለሜን ሰርግ እንድታበላሽ ይጠይቃታል እናም አጥናፍ ለእሱ ሲሆን ምንም እንቢ ስለማትል ታደርገዋለች።
  2. ለሌሎች አክብሮት አለማሳየት፦ አገባሻለው ብሎ ያሳመናትን መክሊትን ሌላ ሴት ላይ አይኑ ሲያርፍ ወድያው ይረሳታል። የመክሊትን ክብር ወስዶ የሰራተኛ ልጅ ስለሆነች ምንም አታመጣም ብሎ ወደጎን ገፍትሯታል።
  3. ራስን መቆጣጠር አለመቻል: መኳንንት ስሜቱን መቆጣጠር አይችለም። ከአዬሁ ጋር ግንኙነት ለመመስረት እንዲችል ከአሌሜ ጋር ያለውን ቃልኪዳን ለማቋረጥ በድጋሜ እናቱ እንድትረዳው ይጠይቃታል። ህይወቱን ሙሉ የሚፈልገውን ስታደርግ የኖረችው አጥናፍ አሁንም ጣልቃ ገብታ ትረዳዋለች።
  4. የግንኙነት ችግሮች ከእነዚህ ሶስት ሴቶች ጋር ያለውን ግንኙነት የሚጀምረው በውሸት በተሞላ መንገድ ነው። አለሜን ከእጮኛዋ በማጣላት እና አየሁን በማስከር እና የቤተሰቧን ማንነት በመደበቅ።

የአጥናፍ ከልክ ያለፈ ልቅነት መኳንንት እንደ ኃላፊነት፣ አመስጋኝነት እና ለሌሎች አክብሮት ያሉ አስፈላጊ የሕይወት ክህሎቶችን ለማዳበር ዕድሉን ሰርቆታል። አጥናፍ መኳንንት እያደረጋቸው ያሉት ነገሮች እየጠቀሙት እንዳልሆነ የምትደርስበት ይመስልዎታል? መኳንንትስ እነዚህን ነገሮች አቁሞ መቀየር ይችል ይሆን?

ይበልጥ ለመመልከት #ሐምዛ ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 3፡00 በ #አቦልቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት! በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed