የመክሊት ህይወት በፍቅር እና በልብ ስብራት የተሞላ ነው። መጀመሪያ የምታፈቅረው መኳንንት እንደማይወዳት ትረዳለች፣ ቀጥሎ እጮኛ ያላት ጓደኛዋን ማግባት እንደሚፈልግ ትሰማለች፣ በተጨማሪም ለእሷ ግድ እንደሌለው እና እሱን መለመን ከአፋፍ እንደሚያስገፈትራት ታውቃለች። የመክሊት የፍቅር ህይወት በእንባ እና ጣጣ የተሞላ እንደሆነ እናውቃለን። ነገር ግን አሁን ደግሞ ይሄን ሀዘን የተሞላ ታሪክ ትታ ከዚህ የተሻለ ኑሮ እንድትኖር የሚያደርግ እድል ይቀርብላታል።
መኳንንት መክሊትን በጭካኔ ወደ ወንዝ ውስጥ ሲገፈትራት ሳትሞት ያዳናት የልጅነት ጓደኛዋ ክንዴ ነበር። ክንዴ ሌላ አካባቢ ያደገ ሲሆን፣ ከዚህ ክስተት በፊት ለመክሊት ልዩ ስሜት አልነበረውም ነገ። ነገር ግን የመክሊትን ህይወት ካተረፈ በኋላ እሷን ማፍቀር ይጀምራል። ከዛ ጊዜ በኋላ ክንዴ እና መክሊት አብረው ብዙ ጊዜ ያሳልፋሉ፣ ክንዴም ይበልጥ ከመክሊት ፍቅር ይይዘዋል። እናም ክንዴ አላስችል ብሎት መክሊት እንድታገባው ይጠይቃታል ነገር ግን መክሊት ይህ መሆን የማይችልበት ምክንያት እንዳላት አሳውቃ አይሆንም ትለዋለች።
የክንዴ የጋብቻ ጥያቄ ለመክሊት የፍቅር ህይወት ጥሩ ይሆናል ብለን ስናስብ መክሊት አይሆንም ብላለች። ግን ልምን? ይሄን ጥያቄ እናቷ ስታቀርብላት፣ መክሊት ያጋለጠችው ነገር በጣም አስደንጋጭ ነበር። መክሊት ከመኳንንት አርግዛለች። በገጠር ውስጥ ለምትኖር ሴት ይሄ የህይወት አቅጣጫዋን በጎጂ መንገድ የሚቀይር ነው። ስለዚህ በእርግዝናዋ ምክንያት የመክሊት አለም ማነስ ጀምሯል፣ በቀጣይ የምትመርጣቸው ነገሮች እራሷን እና ልጇን የሚጠቅም መሆን አለባቸው።
ስለዚህ አሁን ምን ማድረግ ትችል ይሆን?
መኳንንትስ ስለ እርግዝናዋ ቢሰማ በሰላም እንድትኖር የሚፈቅድላት ይመስልዎታል? ወይስ ምስጢሩን ለመደበቅ ብሎ ወንዙ ዳር የጀምረውን ይጨርሳል?
ታሪኩን በ #ሐምዛ ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 3፡00 በ #አቦልቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!