channel logo
Afaf S1

የእስከዳር የተለያዩ ባህሪዎች - አፋፍ

ዜና
14 ዲሴምበር 2023
እናት፣ ሚስት፣ አሳዳጊ፣ ጠላት እና አለቃ ነች።
afaf eskedar article

እስከዳር መታፈሪያ ለአፋፍ ገጸ ባህሪያት ብዙ ነገር ነች። እናት፣ ሚስት፣ አሳዳጊ፣ ጠላት እና አለቃ ነች። እስከዳር እነዚህን ሁሉ ሆና ግን አንድ ነገር ብቻ ነው የምትፈልገው እናም ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በላይ የምታስቀምጠው አንድ ነገር ህልሟ ነው። እስከዳር ለህልሟ ስትል እነዚህን ገጸ ባህሪያትን በድላለች

እንቆጳ

እንቆጳ በእስከዳር እጅ ብዙ አጥታለች። በህጻንነት እስከዳር አውጥታ አፋፍ ላይ ትታት ጠፍታለች። አቶ ዋሲሁን እንቆጳን ከአፋፍ አንስቶ እንደ እራሱ ልጅ አሳድጓታል በተጨማሪም ቃል የገቡትን ለማስፈጸም ሲሉ በጂኦሎጂ ትምህርት እንድትማር አድርገው ነበር። ነገር ግን አቶ ዋሲሁን ስለ ኦፓሉ እውነቱን ለእንቆጳ ሳይነግሯት በእስከዳር እጅ ህይወታቸው ተቀጭቷል። እንቆጳ የወላጅ እናቷን ብቻ ሳይሆን ያጣችው፣ አሳዳጊ አባቷንም በእስከዳር እጅ ለእስከዳር ህልም ሲባል አጥታለች።

ፍርቱና

የፍርቱና ጥፋት የእስከዳርን ወንጀል ማወቅ ነበር። ነገር ግን በዚህ ብቻ ህይወቷ ይመሰቃቀላል፣ ቤቷ ይቃጠላል፣ ፍቅረኛዋን ታጣለች፣ ፈንጂ ይላክባታል፣ በጥይት ትመታለች፣ እስር ቤት ትገባለች እናም እናቷ ትጎዳባታለች። ይህ ሁሉ የተፈጠረው ፍርቱና የእስከዳርን ወንጀል በማወቋ እና ላለማጋለጥ ክፍያ በመጠየቋ ነበር። ወንጀሉን አለማጋለጧ ትክክል ባይሆንም፣ ፍርቱና ለእስከዳር ህልም መሳካት በጣም ተጎድታለች።

ዳግም

ዳግም የእናቱን ንጽህና እና ጥሩ መሆን ብቻ ነው የሚያውቀው ነገር ግን የእናቱ ሂወት እንዲሳካ ብዙ መሰዋትነት እንዲከፍል ተገዷል። ከአፋፍ ኦፓሉን ለማግኘት የሚያስፈልጋት ፍቃድ የጌታቸው እጅ ውስጥ ነበር እናም እሱ የሚፈልገው ልጁ ኢታንያ ከዳግም ጋር እንድትጋባ ነበር። እስከዳር ለህልሟ የማታደርገው ነገር የለም እና ዳግምን ከኢታንያ ጋር ለማጋባት ስትገፋፋው ትቆያለች። ይህ እቅዷ ቢበላሽም፣ ዳግም ስለ እናቱ ወንጀል እውነቱን አውቋል። ይህ ለዳግም የሚያስጨንቅ ምርጫ ያቀርብለታል፣ እናቱን ለፖሊሶች አሳልፎ መስጠት ወይም  ምስጢሯን መደበቅ።

እስከዳር ከእነዚህም በላይ በጣም የጎዳቻቸው ገጸ ባህሪያት አሉ ነገር ግን እስካሁን ለጥፋቷ ቅጣት አላገኘችም። ትልቁ ህልሟም በአፋፍ ላይ ያለውን ኦፓል ማደን እና ልጇን እና ፍቅሯን አስልፋ የሰጠችበትን ህልም ማሳካት ነው። የእስከዳር ህልም በመጨረሻ ይሳካል ወይስ የምትጎዳቸው ሰዎች ከመጠን በላይ መብዛት ይቀጥላሉ?

#አፋፍ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉ!