የገላ ቤተሰብ በተከለከለ ፍቅር ምክንያት አንድ መሆን አልቻለም። ቃልአብ ለፀሀይ ያለው ፍቅር ከእናቱ ጋር አጣልቶት ከቤት ወጥቶ ከጓደኞቹ ጋር መኖር ከጀመረ ብዙ ጊዜ አልፎታል። እናቱ ገላ ለልጇ ያላትን ናፍቆት ደብቃ ከሌሎች ልጆቿ ጋር እየኖረች ነው ነገር ግን ህክምና የሌለው በሽታ ሲይዛት እውነቱን ለመናገር ትገደዳለች። ይህ ፀሀይን ከሚያፈቅራት ልጇ ግሩም ጋር ያጣላታል እናም እሱ ከቤት ይጠፋል።
ገላ የልጆቿን አንድነት ማየት ስትፈልግ ልጆቿ ይበልጥ እየተበተኑ ይመጣሉ። ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ ቤተሰቡ አንድ ቤት ውስጥ ተገኝቷል፣ ይህ ማለት ታርቀው አብረው ይኖራሉ ማለት ይሆን? በመጨረሻው የናፍቆት ድራማ ክፍል ላይ ታሪኩን ይከታተሉት!
እርስዎ ስለ ገላ ቤተሰብ የሚያውቁትን ጥያቄዎችን በመመለስ እውቀትዎን ይፈትኑ!
ናፍቆት ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ዱካ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 እንዳያመልጥዎ!