abol tv logo

ከተወዳጇ የአቦል ቲቪ ተዋናይ ሜላት ተወልደ ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ

ዜና
21 ኦክቶበር 2024
ተዋናይት ሜላት ተወልደን እንተዋወቃት።
melat tewolde article

በአቦል ቲቪ አንዴም ወይም ሁለቴም ብቻ ሳይሆን አምስት ጊዜ በተለያዩ ድራማዎች ምርጥ ብቃቷን አሳይታለች። በመጀመሪያው የአቦል ቲቪ ተወዳጅ ድራማ አደይ ላይ የራሄልን ገጸ ባህሪ ስትጫወት የተዋወቅናት ተዋናይት በማራኪ ብቃቷ አስደምማናለች። እኛም ተመልካቾች ሜላት መጠየቅ የሚፈሉጉዋቸውን ጥያቄዎችን አቅርበንላታል። ይበልጥ ስለ ተዋናይት ሜላት ተስፋዬ ለማወቅ ማንበብ ይቀጥሉ።

  1. በተለያዩ የአቦል ቲቪ ፕሮጀክቶች ላይ የነበረሽ ስራ ጊዜ እንዴት ነበር?

በጣም ቆንጆ ኤክስፒሪያንስ ነበር! በዲኤስቲቪ እና አቦል ቲቪ የመጀመሪያ ስራዬ አደይ ነበር ከዛ በመቀጠል የውሃ ሽታ፣ ሰባውያን፣ ሀምዛ እና የልቤ ላይ አራት ወይም አምስት ክፍል ላይ ሰርቻለሁ። ሁሉም ላይ የተለያየ አይነት ኤክስፒሪያንስ ነበረኝ እና ትወናዬን ቀን በቀን እንዳሻሽል አድርጎኛል፣ በጣም አሪፍ ኤክስፒርያንስ ነበረኝ።

  1. በሀምዛ ድራማ ላይ አነጋገርሽን ቀይረሽ ያቀረብሽው ትወና በጣም ማራኪ ነበር፣ ምን ያህል ይከብድ ነበር?

ዲኤስቲቪ አቦል ቻናል ላይ የሰራኋቸውን ስራዎች በጠቅላላ እወዳቸዋለሁ፣ ለእኔ አሪፍ ኤክስፒሪያንስ ነበሩ። አደይ ድራማ እኔን ከሰው ጋር አስተዋውቆኛል በጣም እወደዋለሁ ነገር ግን ሀምዛ የተለየ ነው ለኔ ምክንያቱም ፈትኖኛል። ከእኔ ሙሉ ለሙሉ የተለየ ነው ኤክስፒርያንስ የነበረው፣ ምንም ጭራሽ የማላቀው ነገር ነው ገጠርም ሄጄ አላውቅም ነበር እና አሪፍ ነበር ኤክስፒሪያንሱ።

ከብዶኝ ነበር እውነት ለመናገር፣ ያን ያክል ባይባልም ትንሽ ገጸ ባህሪዋን እስከምላመዳት ድረስ ከብዶኝ ነበር። ነገር ግን ቢኒያም ጆን በደንብ አድርጎ ነው እንድሰራት ያደረገኝ በጣም አግዞኛል፣ ሙሉ ክሩ አግዞኛል እና ሀምዛ ለእኔ ትልቅ ስራ ነበር።

  1. በአደይ፣ የውሃ ሽታ፣ ሀምዛ፣ የሳባውያን እና የልቤ ድራማዎች ላይ ከተወንሻቸው ገጸ ባህሪያት ሁሉ የማን ገጸ ባህሪ ካንቺ ጋር ይቀራረባል?

አደይ፣ ሀምዛ እና የልቤ ላይ ያሉት ገጸ ባህሪዎች ከእኔ ባህሪ ጋር አይቀራረቡም። ሰባውያን ላይ ያለችው ገጸ ባህሪ ትንሽ ከእኔ ጋር ትቀራረባለች ግን የውሃ ሽታ ላይ ያለችው ገጸ ባህሪ ከእኔ ባህሪ ጋር ይበልጥ ትቀራረባለች ብዬ አስባለሁ።

  1. ለጀማሪ ተዋናዮች ምን አይነት ምክር አለሽ?

ያን ያህል ለመምከር ደርሻለው ብዬ አላስብም እኔም ብዙ መቀበል ያለብኝ ነገሮች አሉ። ነገር ግን ካለሽ ላይ የምትሉኝ ከሆነ፣ አንድ ሰው መሆን የሚፈልገውን ነገር ካወቀ በመጀመሪያ ደረጃ እና ከዛ ለዛ ነገር ከሰራ፣ ከጣረ፣ የምሩን ከልቡ ፕላን ቢ አድርጎ ሳይሆን ፕላን ኤ አድርጎ ከሰራ የሚፈልግበት ቦታ የማይደርስበት ምክንያት አለ ብዬ አላስብም። ስለዚህ ተዋናይ መሆን የምንፈልግ ከሆነ መጀመሪያ እውነት ይሄንን ነው የምፈልገው ብሎ እርግጠኛ መሆን በእራስ ከዛ ለእዛ ነገር እስከመጨረሻው ጊዜ መፋለም። ከዛ እግዝያብሔርም ሲረዳ ቀላል ነው።

  1. ለ24 ሰዓት አንድ የአቦል ቲቪ ገጸ ባህሪ ሆነሽ መኖር ብትችይ የማንን ገጸ ባህሪ ትመርጫለሽ?

ለ24 ሰዓት ሀምዛ ድራማ ላይ ያለችውን መክሊትን ሆኜ ኤክስፒርያንስ ለማድረግ እሷን መሆን እመርጣለሁ።

  1. በአቦል ቲቪ ድራማዎች ላይ እየተወንሽ ካልሆነ ሌላ ምን እያደረግሽ ጊዜሽን ታሳልፊያለሽ?

ሌላ ስራዎችን እየሰራሁ እና ፊልም እያየሁ ጊዜዬን አሳልፋለሁ።

  1. በአሁን ሰዓት ከሚቀርቡት የአቦል ቲቪ ድራማዎች የትኛውን ወደሽዋል?

የእሳት እራት

ከሜላት ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ ይሄን ይመስል ነበር! እናንተ ሜላት ከቀረበችባቸው ድራማዎች የቱን በጣም ይወዱታል?

የሜላትን አዲሱን ስራ በ የልቤ ዘወትር አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት።

 #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉhttps://tinyurl.com/yc8p3xvd እና DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed