Logo

በሰኔ ወር በአቦል ቲቪ እነዚህ ይመልከቱ!

ዜና
27 ጁን 2024
እነዚህን ምርጥ ድራማዎች በአቦል ቲቪ ይከታተሉ።
what to watch june 2024

በዚህ ወር አቦል ቲቪ አዲስ አስደሳች ትርዒቶችን ይዞ ቀርቧል እናም ይበልጥ ድራማዎችን መጠበቅ ይችላሉ። በአቦል ቲቪ ማየት የሚችሏቸው ትርዒቶች እነዚህ ናቸው፡

አፋፍ

የአፋፍ ታሪክ ልብ አንጠልጣይ ነው። አብዮት በመጨረሻ ሽቱ ለረጅም ጊዜ የጠፋችውን ልጁን በተመለከተ አንድ ነገር እንደምታውቅ መጠራጠር ይጀምራል። ሽቱ በመጨረሻ እውነቱን ትናገር ይሆን? አፋፍ ዘወትር ከሰኞ- ረቡዕ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ላይ አያምልጥዎ።

ሐምዛ

መኳንንት አየሁን ስለቤተሰቧ ውሸት ነግሯት ሊቀርባት ይጀምራል። መኳንንት አየሁን ከቤተሰቧ ለመደበቅ ቢሞክርም በመጨረሻ ቤተሰቧን ታገኛቸው ይሆን? ሐምዛ ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 3:00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይመልከቱ።

የረቂቅ መንገድ

አቶ ገዛህኝ መሳይ ከበሉ ጋር ስላለው የፍቅር ግንኙነት ሲሰማ የማይቻል ምርጫ ለመሳይ ያቀርብለታል። አቶ ገዛህኝ የቤቱ ሰራተኛ ከሆነችው ነፍሰ ጡር ፍቅረኛው በሉ ጋር አብሮ መሆን ወይም ለድርጅቱ መስራት መካከል መሳይ እንዲመርጥ ይፈልጋል፣ መሳይ ምን ይመርጣል? የረቂቅ መንገድ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ።

ሰራተኛ ፈልጉልን

አዲስ ባለትዳር ሱዚ እና ዜና በግንኙነታቸው ላይ ለማተኮር ሲወስኑ በቤት ውስጥ ያለ ስራ ላይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ይገባቸዋል። ስለዚህም ሰራተኛ ለመቅጠር ይስማማሉ ነገር ግን ሰራተኛ መቅጠር ቀላል ሥራ እንዳልሆነ ቶሎ ይረዳሉ። ሰራተኛ ፈልጉልን አስቂኝ ድራማ ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት።

ያለ’ለት

በ 5 ኛው የግንኙነት ዓመታቸው ላይ ሩት በድንገት ግንኙነቱን አቋርጣለች እናም አብርሃም ለምን እንደሆነ ለማወቅ እየታገለ ነው። ይህ እየሆነ አንድ የቀድሞ ጓደኛ ወደ አብርሃም ሕይወት ትመለሳለች እናም ጓደኝነት በላይ የምትፈልገው ነገር ያለ ይመስላል። ያለ’ለት ልብ አንጠልጣይ ድራማ ረቡዕ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት።

በምክንያት

አራት ኮሌጅ እያሉ የሚተዋወቁ ጓደኞች ከተመረቁ በኋላ አብረው ለመኖር ይወስናሉ። ታሪኩ ጎልማሳ መሆን ምን ማለት እንደሆነ ሲማሩ እና የሚያጋጥሟቸው ልዩ ክስተቶችን አስቂኝ ጉዞዋቸውን ይከተላል። በምክንያት ኮሜዲ ድራማ ሐሙስ፣ ሰኔ 20 ከምሽቱ 3፡00 ጀምሮ በአቦል ቲቪ ይመልከቱት!.

ሰባዊያን

አንድ የሰላዮች ቡድን የተሰረቀ ቅርስ ለባዕድ ከመሸጡ እና ከአገሩን ወጥቶ መጥፋቱ በፊት እንዲያገኙት ተልዕኮ ይሰጣቸዋል። ተልዕኮአቸውን ያከናውናሉ? ሰባዊያን በአቢል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 አርብ፣ ሰኔ 21 ከምሽቱ 2፡00 እንዳያመልጥዎ።

ምስኪኖቹ ምዕራፍ 4

በመጨረሻም ተወዳጁ ኮሜዲ ምስኪኖቹ አርብ፣ ሰኔ 21 ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ ወደ አቦል ቲቪ ይመለሳል። ታሪኩ በአንድ ቤት ውስጥ በሚኖሩ እርስ በእርስ ለመግባባት ባልቻሉት የአማቶች ኤዱ እና ሙሌ አስቂኝ ጉዞን ይከተላል። ሚስኪኖቹ አርብ፣ ሰኔ 21 ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ።

እነዚህ እና ይበልጥ አስደሳች ድራማዎችን በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉ።