Logo
Afaf S1

ለሚታመንበት ነገር ምን አይነት እርቀት ይኬዳል? የእንደ አንድ ገጸ ባህሪያት መልስ።

ዜና
13 ሜይ 2024
እንደ አንድ ድራማ ዛሬ ማታ ይጠናቀቃል። እንደ አንድ ድራማ በአንዲት ፍቅርተ የተባለች ሴት የህይወት ታሪክ ላይ ያጠነጥናል። ፍቅርተ በመስራቤቷ ሙስና ሲፈጸም በመናገሯ ተጨቁና ድምጿን በሆነ መንገድ ለማሰማት ስትሞክር ለአዲስ አበባ ኗሪዎች ገንዘብ የሚበትን ቡድን ጋር ትቀላቀላለች። ይህ ቡድን ያጣውን ማህበረሰብ ገንዘብ እየበተነ በመርዳት እና ሌሎች የእርዳታ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ። ግን ፍቅርተ ይሄን ቡድን ስትቀላቀል ከቡድኑም ከቤተሰቧም መደበቅ የነበሩባት ነገሮች ነበሩ።

ፍቅርተ እና በዙሪያዋ ያሉት ሰዎች ለሚያምኑበት ነገር ምን እንደሚያደርጉ እንስማ።

ለምታምኑበት ነገር እስካሁን ምን አድርጋችኋል?

ፍቅርተ፡ ለማምንበት አቋም ብዬ ቤተሰቤን ዋሽቻለው በተጨማሪም የእንቅልፍ መዳኒት እየሰጠዋቸው በለሊት ወደ ስብስባ ሄጃለው። ስለ ቤተሰቤም ዋሽቻለው። ለተፈሪ እንዳላገባሁ እና እንዳልወለድኩ የነገርኩት ቤተሰቤን ለመጠበቅ ብዬ ነበር ግን አሁን ይሄ ውሸት ነገሮችን አወሳስቧል። በአንድ በኩል ተፈሪ ውሸታም እንደሆንኩ እና ለአቶ ማንደፍረው እየሰለልኩ ብሎ ነው የሚያምነው፣ በሌላ በኩል ደግሞ ልጄ ሳምን ስብሰባ ስሄድ በማየቷ ምስጢሬን ለማወቅ እየተቃረበች ነው። ተፈሪ የማይሆን ነገር ሳያደርግ ነገሮችን ማስተካከል እፈልጋለሁ።

ተፈሪ፡ ለማምንበት አቋም ብዬ ምንም ከማድረግ ወደኋላ አልልም። ይሄን ቡድን የመሰረትኩት ሀብታሞች ከበቂ በላይ ኖሯቸው እየኖሩ ሌላው ህዝብ እየተቸገረ ማየት ስላልፈለኩ ነው። ገንዘብ በመበተን የተቸገረው ህዝብ ህይወት ላይ ለውጥ ማምጣት ችለናል ግን ከዚህም በላይ ማድረግ እፈልጋለሁ። አዎ የጓደኛዬ ስዩምን ልጅ አግቸዋለው እና እሱ እቅዳችንን እንደሚያደናቅፈው ምንም ጥርጥር የለኝም ስለዚህ ያደረኩት ትክክል ነው ብዬ አምናለሁ። ለማምንበት ነገር ብሎ ሞት ቢመጣም እቀበለዋለሁ።

በረከት፡ ለማምንበት አቋም ብዬ ምን አደርጋለሁ? ከባድ ጥያቄ ነው ይሄ። በስራዬ እና አለቃዬ ስለተማመንኩ ሚስቴ የምትመክረኝን አልሰማሁም። ይህ ደግሞ ከአለቃዬ እህት ጋር ያልሆነ ግንኙነት እንዲኖረኝ እና ስራዬን ማጣት ፈርቼ ያላመንኩባቸውን ነገሮች እንድቀበል አድርጎኛል። በርግጥ እነዚህ ክስተቶች የአለቃዬን ትክክለኛ ማንነት እንዳውቅ አድርጎኛል እናም ያየሁት ነገር አስፈሪ ነበር።

ያደረጋችኋቸውን ነገሮች ተጸጽታችሁባቸዋል?

ፍቅርተ፡ እርግጠኛ አይደለሁም፣ እርስዎ በእርግጠኛነት እንዲያውቁ የእንደ አንድን የመጨረሻ ክፍል ዓርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ዱካ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 እንዳያመልጥዎ!

ተፈሪ፡ በዛሬ ማታው የእንደ አንድ ክፍል ይወቁ።

በረከት፡ ዛሬ ማታ መልሱን እናውቃለን።

ከእንደ አንድ ገጸ ባህሪያት ጋር ቆይታችን ይሄን ይመስላል።

እርስዎ የእንደ አንድ ገጸ ባህሪያ በምርጫቸው ተጸጽተዋል ብለው ያምናሉ?

አዎ ተጸጽተዋል

አይ አልተጸጸቱም

የእንደ አንድን የመጨረሻ ክፍል አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 ይከታተሉት! በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed