abol tv logo

"አቦል ዱካ 466 ቻናል" ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ስርጭቱ ይቋረጣል

ዜና
05 ሴፕቴምበር 2024
"አቦል ዱካ 466 ቻናል" ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ስርጭቱ የሚቋረጣል
Abol Duka closed

ውድ ተመልካቾቻችን!

የላቁ ይዘቶችን ለደንበኞች ለማቅረብ ዘወትር የሚተጋው የአፍሪካ ግዙፉ የመዝናኛ ይዘቶች አቅራቢው መልቲቾይስ አፍሪካ ሆልዲንግስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞቹ አዳዲስና ምርጥ ሀገርኛ ይዘቶችን በማቅረብ ላይ ይገኛል።

የዚህ ጥረቱ አካል የሆነውና ሁሉም የዲኤስቲቪ ደንበኞች ተወዳጅ ሀገርኛ የመዝናኛ ይዘቶችን እንዲመለከቱ በማሰብ ፤ ከፍ ካለው የ "ሜዳ ፓኬጅ" ጀምሮ ይሰራጭ የነበረውን ተወዳጁን አቦል ቴሌቪዥን ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ ሁሉም የዲኤስቲቪ ፓኬጆች ላይ እንዲሰራጭ ተደርጓል። በዚህም በርካታ ደንበኞቻችን ደስተኞች ሆነዋል።

በመሆኑም ለደንበኞች አስቀድመው የተሰራጩ የአቦል ይዘቶች በድጋሚ ለጎጆ ፓኬጅ ደንበኞች ሲተላለፉበት የቆየው "አቦል ዱካ 466 ቻናል" ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ስርጭቱ የሚቋረጥ ሲሆን አዳዲስና ተወዳጅ ሀገርኛ ይዘቶችን በተወዳጁ አቦል ቻናል 465 ላይ ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ እንድትመለከቱ በአክብሮት እንገልፃለን።