Logo
Afaf S1

የአፋፍ ገጸ ባህሪዎች የቀረቡላቸው 3 ምርጫዎች፣ ምርጫቸውን እንዲያደርጉ ይርዷቸው!

ዜና
24 ኦክቶበር 2023
የአፋፍ ገጸ ባህሪዎች ከባድ ምርጫዎች ቀርበውላቸዋል፣ ምን ይመርጡ ይሆን?
afaf article - choices

በአፋፍ ላይ የምንመለከታቸው ታሪኮች መሳጭ እና ልብ አንጠልጣይ ናቸው። በተጨማሪም ታሪኩ በአፋፍ ገጸ ባህሪያት ህይወት የደመቀ ነው። ነገር ግን በፍቅር የምንመለከታቸው የአፋፍ ገጸ ባህሪያት ትልቅ ምርጫዎች ቀርቦላቸዋል። ምርጫቸውን እንዲያደርጉ ሊረዷቸው ይችላሉ? ይበልጥ በማንበብ ይርዷቸው።

የዳግም ምርጫ

ዳግም በፍርቱና መጥፋት ምክንያት ጊዜውን በሀዘን ነው እያሳለፈ የቆየው። በዚህ መሀል ኢታንያ ሁሌም ከአጠገቡ ሆና ልትደግፈው ትሞክራለች። የዳግም ሀዘን አልዋጥ ያላት እናቱ ግን ስለ ሁለቱ ወጣቶች ግንኙነት የሆነ ነገር ማድረግ ትፈልጋለች። ስለዚህም ዳግም እና ኢታንያ እንዲታጩ ታደርጋለች። ይህ የእስከዳርን እና ኢታኒያን ህልም ቢያሳካም፣ የዳግም ፍላጎት ተቃራኒ በመሆኑ ጭንቀት ውስጥ ከቶታል።

afaf s1 poll
afaf poll 5

ዳግም ኢታኒያን እንደማያገባት ቢነግራት ይሻላል?

አዎ መንገር አለበት 77%
አይ ባይነግራት ይሻላል23%

የአዲስ (ኮብራ) ምርጫ

ኮብራ ነፍስ ካወቀ ጀምሮ እጁ ከሌብነት አለም ውስጥ ተነስቶ አያውቅም። በአንድ ወቅት የቤተሰቡን ምክር ሰምቶ ትክክለኛ ስራ መስራት ከጀመረ በኋላ የድሮ ጓደኛው ጎሚት መፈታት ሁሉንም ይቀይራል። ከጎሚት ጋር እያቀደ የነበረው ዘረፋ እራሱን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡንም አደጋ ውስጥ ይከተዋል። በዚህ ምክንያት ከእስርቤት ሲወጣ ደግሞ ወደዛ አለም እንደማይመለስ ይወስናል። ነገር ግን ለዘረፋው ቀብድ የከፈለው አሌክስ ኦፓል ቤቱ ድረስ መጥቶ ቀብዱን ይጠይቃል።

afaf s1 poll
afaf poll 6

ኮብራ እውነቱን ለቤተሰቡ ተናግሮ ቀብዱን ለመመለስ ይሞክራል ወይስ እንደታዘዘው ኦፓሉን ከእስከዳር ይሰርቃል?

እውነቱን ይናገራል73%
ኦፓሉን ይሰርቃል27%

የቹቹ ምርጫ

ቆንጂት እና ቹቹ ፍቅራቸውን በድብቅ ሲያጣጥሙ ኖረዋል ነገር ግን አሁን የቆንጂት ውሳኔ ለዘላለም ሊያለያያቸው መጥቷል። በድህነት የተማረረችው ቆንጂት ፀጉር ቤቷን ሸጣ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ወስናለች ነገር ግን ይህ ማለት ከቹቹ ጋር ያላት ግንኙነት ያበቃል ማለት ነው። ቆንጂት ፀጉር ቤትዋን ለመሸጥ የቹቹን እርዳታ ጠይቃለች።

afaf s1 poll
afaf poll 7

ቹቹ የሚያፈቅራት ሴት እንድትለየው የሚያደርጋትን ነገር ያደርጋል?

ቹቹ ጸጉር ቤቱን ለመሸጥ ይረዳታል21%
ጸጉር ቤቱን መሸጥ መርዳት ያቅተዋል79%

የአፋፍን ተወዳጅ ገጸ ባህሪያት ምርጫቸውን እንዲያደርጉ በመርዳታችሁ እናመሰግናለን! እርስዎ የመረጡላቸውን መንገድ የሚከተሉ ከሆነ በአፋፍ ድራማ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉ!