እስካሁን በአስኳላ ትምህርት ቤት ሲቀርብ የነበረው የየኔታ የትምህርት ጉዞ አስተማሪ እና አስቂኝ ጊዜያቶችን አስቃኝቶናል። ይሄን ታሪክ ያደመቀው የየኔታ ልዩ የህይወት እይታ እና የአስታማሪዎች ተቃራኒ ባህሪ ነው። ከእነዚህ ልዩ ገጻ ባህሪያት ድርጊቶች በምዕራፍ 3 በጣም አስቂኝ የምንላቸው ጊዜያቶች ይሄን ይመስላሉ።
- “ደስተኛ ሚስት ደስተኛ ይህወት!”
ይሄን አባባል አጥብቆ የሚከተለው ይነበብ የተባለው የአስኳላ አስተማሪ፣ ለሚስቱ ደስታ ብሎ አረብኛ ለመማር ሞክሮ ነበር። ስለ ይነበብ ባህሪ ከምንወደው ነገር አንዱ፣ ፈተናዎችን ተቀብሎ እያዝናናን መጋፈጥ መቻሉ ነው። ስለዚህም ሚስቱ በአማርኛ ሲያወራ ደስ አንደማይላት ስታሳውቀው እሺ ብሎ ሌላ ቋንቋ ለመማር መነሳቱ በጣም አስደስቶናል።
ይነበብ አረብኛ ለሚስቱ ሲማር ይመልከቱ፡
- “የዜሮ ቦታ ምንድን ነው?”
የኔታ በክፍል ጊዜ የሚያቀርቡት ወጣ ያሉ ጥያቄዎች የተለመዱ ናቸው። በሒሳብ ክፍል ጊዜ ላይ ላቀረቡት ጥያቄ አስተማሪ ኮዬ መልስ መስጠት ባለመቻላቸው ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት ያቅዳሉ። የሰላማዊ ሰልፉ ምክንያት ደግሞ የዜሮ ቁጥርን ቦታ ለማግኘት ነበረ። ለየኔታ ጥያቄ ለየት ያለ መልስ የነበራቸው ኮዬ በጣም አዝናንተውን ነበር።
የኮዬን ሰላማዊ ሰልፍ ይመልከቱ፡
- 'ቀኑ በጣም ደስ ይላል'።
በላቸው አጨናቂ ጊዜ ሲገጥመው ሚስ አዩ በሰጠችው ምክር ህይወቱ በመቀየሩ የሚስ አዩ ዩ ቱብ ቻናልዋ ላይ ቀርቧል። ይህ ምክር ግን በሁልም ተቀባይ አይደለም በዚህ ምክንያት ከተቃዋሚዎች አንዱ አስተማሪ ወገኔ የዩ ቱብ ቆይታቸው ይረብሻል። መምህር ወገኔ የሰጣቸው አስተያየቶች በጣም አዝናንቶን ነበር።
የወገኔ እና በላቸውን መስተጋብር ይመልከቱ፡
ሌሎች የአስኳላ አስቂኝ ጊዜያትን እዚህ መመልከት ይችላሉ፡
እርስዎን በጣም ያዝናናዎት ክስተት የትኛው ነበር? በማህበራዊ ሚዲያችን ኮመንት በማድረግ ያሳውቁን።
አስኳላ ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ 466 ይከታተሉ!