Logo
Askuala S2

አስኳላ ምዕራፍ 2 በአስቂኝ ሁኔታ ተጀምሯል! - አስኳላ

ዜና
16 ሴፕቴምበር 2021
በላቸው እምወድሽን ለማስመዝገብ ይሞክራል።

ተወዳጁ የአቦል ቲቪ ኮሜዲ አስኳላ ከአጭር እረፍቱ በኋላ ወደ ቻናሉ ተመልሷል። ያለፉት አስኳላ ክፍሎች ላይ የአስኳላ አስተማሪዎች የኔታ ትምህርት ቤት መማር እንዲያቆሙ ብለው ባለቤታቸው እምወድሽን ለማስመዝገብ ይሞክሩ ነበር።

በዚህ ሳምንት የቀረበው አዲሱ ክፍል ላይ የኔታ የባለቤታቸውን መመዝገብ እንደሚቃወሙ ተረድተናል። እምወድሽ የኔታ ትምህርት በጀመራቸው ሌሎች ነገሮችን በመተዋቸው ቅሬታቸውን አሳውቀዋል።

የአስኳላ ዳይሬክተር በላቸው በትምህርት ቤቱ የሚሳተፉት ተማሪዎች በመቀነሳቸው አስተማሪዎችን ተማሪ የማስመዝገብ ዘመቻ ላይ ይልኳቸዋል። ይሄንን እድል ተጠቅመው የስፖርት አስተማሪው ማዕበል እና ዳይሬክተር በላቸው የኔታ ቤት ይሄዳሉ፣ እምወድሽን ለማስመዝገብ ይስማማሉ።

የኔታ ስለዚህ ሲሰሙ ምን ያደርጉ ይሆን?

አስኳል ኮሜዲ ረቡዕ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉ!